የ “ዝክረ-ፊደል” መርሐግብር አርብ ይደረጋል

- Advertisement -
Sidebar AD

የ”ዝክረ-ፊደል” መድረክ ዘንድሮ ለ4ተኛ ጊዜ አርብ ሚያዚያ 16/2018 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

መድረኩን በተከታታይ ዓመታት እያዘጋጀ የቀጠለው የኢትዮጵያ ማኅበራዊ አጋርነት አበረታች (Ethiopia Social Partnership Advocacy) ሀገር በቀል ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ዘካሪያስ አምደብርሃን እንደገለፁት ዝግጅቱ የኢትዮጵያ ፊደልን ሁለገብ አበርክቶ በመዳሰስ፤ ከማኅበረሰባዊ መገለጫነቱ አኳያ ዓይነተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

በዘንድሮ መርሐግብር ላይ በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡
ፊደል ሁለንተናዊ ሉዓላዊነታችንን በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድ የነበረውንና ያለውን ሚና በተመለከተ በፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያስ የኢትዮጵያ ፊደል ከፀረ-ቅኝ ግዛት ተፅዕኖ የመላቀቅ ተምሳሌትነቱን በፕሮፌሰር አየለ በከሪ፤ ፊደል እንደታሪክ መዝገብነት ምን አበረከተ !የሚለውን በመምህር ዳንኤል ሰይፈ ሥላሴ፤ የኢትዮጵያውያን ፊደል በሌሎች ንፅረተ-ፊደላት ምልከታ በዶ/ር አበባየሁ መሰለ፤ በእለቱ ከሚቀርቡ ጥናታዊ ገለፃዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የፓናል ውይይትና የእውቅና መርሐግብርም ይኖራል፡፡ “በዝክረ ፊደል” በዝግጅት ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ታዳሚያን አርብ ሚያዚያ 16/2018 በወመዘክር አዳራሽ መገኘት እንደሚችሉም ተገልፆአል፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችም በእለቱ ተገኝተው የዘገባ ሽፋን እንዲሠጡ ጥሪ ቀርቧአል፡፡


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: