ጆኒ በ1ኛው ዙር አሸነፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

* የ1 ሚሊዮን ብር የቦነስ ሽልማትም ተረከበ
* የንቃተ ህሊና ድፍረትና ፍልሚያ

#Ethiopia | ​በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ የመጀመሪያው ፕሮፌሽናል የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ድምቀት ተካሂዷል። በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጆኒ ጁጁትና የንቃተ ህሊና ፍልሚያ በጆኒ አሸናፊነት ተደምድሟል።

​ ጆኒ ውድድሩ በጀመረ ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ንቃተ ህሊናን መሬት ላይ ጥሎ በመደብደብ የቴክኒክ ብቃቱን አስመስክሯል። ከድሉ በኋላም “ማርሻል አርቲስት ነኝ የምትሉ ሁሉ አስልፌ እቀጠቅጣችኋለሁ” ሲል በኩራት ተደምጧል።

​ ከቦንጋ ተነስቶ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የቆመው ንቃተ ህሊና፣ ራሱን በኢንተርኔት ቪዲዮዎች አዘጋጅቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሮፌሽናል መድረክ መርገጡ ለብዙዎች መነቃቃትን ፈጥሯል። “ሽንፈት መነሻዬ ነው” በሚል መንፈስ ዳግም እንደሚመለስ ቃል ገብቷል።

​ ጆኒ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ወርቃማ ታሪኩን ጽፏል።

የዳኞችና የአዘጋጆቹ ከጆኒ ጋር ያላቸው ቅርበት እንዲሁም በንቃተ ላይ የታየው የስነ-ልቦና ጫና በውድድሩ ፍትሃዊነት ላይ ጥርጣሬ ፈጥሯል የሚሉ የስፖርት ቤተሰቦች አስተያየት ነበር።

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የተካሄደው የታላቁ የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ፍልሚያ በጆኒ አስደናቂ የበላይነት ተጠናቋል።

መላው አዲስ አበባ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው ይህ መድረክ፣ ለጆኒ ታሪካዊ ድልን አጎናጽፎታል።

ታዛቢዎች ውድድሩ ለውድድሩ ድምቀት የተደረገ “ለኮፍ ለኮፍ” ነው ቢሉም፣ ክስተቱ ግን ለኢትዮጵያ MMA አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።

መሸነፍ መጨረሻ አይደለም፤ ለመቧቀስ መድረኩ ላይ መገኘት ራሱ ድል ነው። ንቃተ ህሊና ፍርሃትንና ግፊትን አሸንፎ መድረክ ላይ መቆሙ የጀግንነት አክሊል ነው። ድ

​ነገ የታሪክ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል!

ውድድሩ በሀገራችን ለሜክስድ ማርሻል አርት (MMA) ስፖርት እድገት አዲስ በር፤ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።

​#getu #MMAEthiopia #JohnnyVsNkate #Nkatehilina #SweetBox #BoxingEthiopia #AdwaVictoryMemorial #MixedMartialArts #ጆኒ #ንቃተህሊና #ፍልሚያ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1