የመቶ አለቃ ለማ አስፋው የሥራ ስኬቶች ተዘከሩ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ በተለይም በእንስሳት እርባታና በምግብ ዘይት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ከፍተኛ አሻራ ያሳረፉት የመቶ አለቃ ለማ አስፋው የሥራ ስኬቶች የሚዘከሩበትና የቤተሰቦቻቸውን የሥራ ቅብብሎሽ ይፋ የሚያደርግ መርሃ-ግብር በዛሬዉ እለት ተካሂዷል።

በዛሬዉ እለት በተከናወነው በዚህ መርሃ-ግብር ላይ የተከበሩ አቶ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ባለሀብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ባለፈዉ የካቲት 4 ቀን 2018ዓ.ም በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸዉ ያለፉት መቶ አለቃ ለማ አስፋው፣ በአየር ኃይል መኮንንነት ካበረከቱት አገልግሎት ባሻገር በግሉ ዘርፍ ”አለማ ፋርምስ” እና ”ሊዮስ የምግብ ዘይት” የመሳሰሉ ግዙፍ ተቋማትን በመገንባት ከ500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠሩ ታታሪ ባለሀብት እንደነበሩ ተገልጿል።

በተጨማሪም መርሃ-ግብሩን ምክንያት በማድረግ “ሊዮስ የምግብ ዘይትና አኩሪ ምርቶች” ድርጅት በቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኘው ”ለየኛ ለኛው የአረጋውያን መርጃ ማዕከል” የ500 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

መቶ አለቃ ለማ አስፋው ከንግድ ሥራቸው ጎን ለጎን በኢትዮጵያ የእንስሳት መኖ፣ የወተትና የዘይት አምራቾች ማህበራት ውስጥ በቦርድ አመራርነት በማገልገል ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የሀገር ባለውለታ እንደነበሩ በዕለቱ ተገልጿል።

በጋቶ ተወልደው፣ በአስመራ ዩኒቨርሲቲ ተምረው፣ በአየር ኃይል አገልግለውና በንግዱ ዓለም ስኬታማ ሆነው ያለፉት እኚህ ሰው፤ ለኢትዮጵያ ወጣቶች “በታታሪነትና በዕውቀት ማንኛውንም ከፍታ መድረስ ይቻላል” የሚል ትልቅ የህይወት ትምህርት ትተው ማለፋቸዉ ነዉ የተገለፀዉ።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: