የሻኪራ የብራዚል የሙዚቃ ዝግጅት በታዳሚ ብዛት የዓለምን ክብረ ወሰን ሰበረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ታዋቂዋ ኮሎምቢያዊት ድምጻዊት ሻኪራ በዓለም ዙሪያ የምታቀርበው ኤል ዶራዶ ዎርልድ ቱር የተሰኘው የሙዚቃ ኮንሰርት በብራዚሏ ሪዮ ዲጄኔሮ ከተማ እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ ተከናውኗል።

በከተማዋ በሚገኘው ኮፖካባና ቢች አቅራቢያ በነፃ በቀረበው በዚህ ዝግጅት ላይ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በአደባባይ በመገኘት የሙዚቃ ኮንሰርቱን ተከታትሏል።

ይህም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች በቀጥታ የታደመበት በመሆን አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

የአራት የግራሚ ሽልማት ባለቤት የሆነችው ሻኪራ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በስፓኒሽ የሙዚቃ ዘርፍ ስሟ የገነነ ሲሆን እስካሁን 12 አልበሞችን ለዓለም አቀፍ አድማጮች አቅርባለች።

የሙዚቃ ስራዎቿም በመላው ዓለም ከ95 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች ተሸጠውላታል።

የ49 ዓመቷ ኮከብ ከቀድሞው የባርሴሎና እግር ኳስ ተጫዋች ጄራርድ ፒኬ ጋር ለ10 ዓመታት የዘለቀ የትዳር ሕይወት የነበራት ሲሆን ሁለት ልጆችንም አፍርተዋል።

ይሁን እንጂ ትዳራቸው ከጥቂት ጊዜያት በፊት በፍቺ መጠናቀቁ ይታወሳል።

መዝናኛ ሚዲያ #meznagnia @meznagnia

#shakira #brazil #concert #recordbreaker #musicnews #entertainment #riodejaneiro #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2