ለቴዲ አፍሮ ኢቶሪካ የሙዚቃ አልበም ግራፊክሱን የሠራው ዳዊት ሰሎሞን ታሰረ።የግራፊክስ ባለሙያው ዳዊት ሰሎሞን በትንትናው ዕለት…

- Advertisement -
Sidebar AD
ለቴዲ አፍሮ ኢቶሪካ የሙዚቃ አልበም ግራፊክሱን የሠራው ዳዊት ሰሎሞን ታሰረ።
የግራፊክስ ባለሙያው ዳዊት ሰሎሞን በትንትናው ዕለት መታሠሩ ተሰምቷል።
ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ኢቶሪካ ለተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም ግራፊክሱን የሠራው ዳዊት ሰሎሞን መሆኑን ዶቼ ቬለ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከቴዲ አፍሮ ጋር ቅርብ የሥራ ግንኙነት ያላቸው የመረጃ ምንጭ ለዶቼ ቬለ እደገለጹት፤ የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ኢቶሪካ የተሰኘው የሙዚቃ አልበም መውጣቱን ተከትሎ ዳዊትን ጨምሮ የታሰሩ ለአርቲስቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ቁጥር ስምንት ደርሷል።
ዳዊት ጓደኞቹ ጋ በሄደበት አጋጣሚ መያዙን የገለፁልን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት የመረጃ ምንጭ፤ እሱ ከመያዙ በፊት ቤቱ በፖሊስ መፈተሹንም ተናግረዋል።
DW
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2