በለውጡ ዋዜማ የሚዲያ ተቋማት በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ነበሩ – ወይዘሮ ኃይማኖት ዘለቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከለውጡ በፊት በኢትዮጵያ የነበሩ የሚዲያ ተቋማት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ነበሩባቸው ሲሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ኃይማኖት ዘለቀ ገለጹ።

እንደ ዋና ዳይሬክተሯ ማብራሪያ ከሆነ በመገናኛ ብዙኃን ዘርፉ ላይ የታዩት ስብራቶች በፖሊሲና በሕግ ማዕቀፎች፣ በመዋቅራዊ አደረጃጀቶች እንዲሁም በተቋማዊና በሙያዊ ሥነ ምግባር የታዩ ጉድለቶች የሚጠቀሱ ናቸው።

መንግሥት እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ጥልቀት ያላቸው የሚዲያ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ አድርጓል።

ከነዚህም ስኬቶች መካከል የባለሥልጣኑ ተጠሪነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሆን መደረጉ፣ የጋራ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋቱ እና ዘርፉ ራሱን በራሱ እንዲመራ የሚያስችሉ የሙያ ማኅበራት ቁጥር እንዲጨምር መደረጉ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የተከናወኑት የሪፎርም ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የሚያሳዩ አሃዛዊ መረጃዎች አቅርበዋል። አጠቃላይ የመገናኛ ብዙኃን ቁጥር ከለውጡ በፊት ከነበረበት 122 ወደ 310 አድጓል።

የሬድዮ ጣቢያዎች ቁጥር ከ52 ወደ 126 ከፍ ሲል፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ደግሞ ከ25 ወደ 128 ደርሰዋል።
በተጨማሪም የሚዲያ የቋንቋ ተደራሽነት ከ39 ወደ 60 ማደጉ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የሚዲያ ምህዳር ሁሉንም አካታች መሆኑን የሚያሳዩት 35 የውጭ መገናኛ ብዙኃን እና 50 የማኅበረሰብ ሚዲያዎች ፈቃድ አግኝተው ወደ ሥራ መግባታቸው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ኃይማኖት ዘለቀ አጽንኦት ሰጥተዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#መገናኛብዙኃን #ሚዲያ #ሪፎርም #ኢትዮጵያ #ዜና #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2