እንኳን ለልደታ ማርያም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

- Advertisement -
Sidebar AD

የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት ቅድስት ድንግል ማርያም🙏

የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ መሆኑን ቅዱሳን መጽሕፍ በሚገባ ያስረዱናል፡፡ አባቷ ንጉስ ሰሎሞን “ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፣ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች” በማለት የተናገረው ትንቢት ሲፈጸም እመቤታችን ከክርስቶስ ልደት በፊት በ15 ዓ.ዓ ግንቦት 1 ቀን በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡ የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን የተናገረውን ቃል መፈጸሙን ሲያመሰጠር “የአናብስት ልጅ አልኩሽ” ይላታል፡፡

“ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ፤ ከአንበሶች ጒድጓድ ወጥተሽ ነዪ፤ ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው፡፡” ይላታል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም “ማርያም ግን ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች” በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል። ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም “የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት” ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን እጅግ በደመቀ ስነ ስርዓት የሚከበርበት ዋነኛው ምክንያት ከዳዊት አካል የቀረችልን ንጽሕት ዘር በመሆኗ ምክንያት ነው፡፡ ቅዱሳን ሐናና ኢያቄም እመቤታችን ስትወለድ ከቤታቸው ወደ ሊባኖስ ተራራ እንደተሰደዱ ገዳማውያን ከዓለም ተሰደዱ፣ ዓለምን ንቀው ስሟን ስንቅ አድርገውም መነኑ።
ገዳማቸውን ስንደግፍ፣ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን።

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1