የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የግል ህክምና አገልግሎት በይፋ መስጠት ይጀምራል።
በግል ህክምና የሚሰጡ አገልግሎቶች ፦
🔹የቀዶ ህክምና አገልግሎት በስፔሻሊሰት እና ሰብ-ስፔሻሊሰት ሃኪሞች
🔹የአጥንት ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የጭንቅላት እና ህብረ-ሰረሰር ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የደም ስር (ቫስኩላር) ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የህፃናት ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የፕላስቲክ እና ሪኮንስትራክቲቭ ህክምና አገልግሎት
🔹የውስጥ ደዌ ህክምና አገልግሎት
🔹የልብ ህክምና (ካትላብ)አገልግሎት
🔹የማህፀን እና ፅንስ ክትትል ህክምና አገልግሎት
🔹የስነ-ልቦና እና ማማከር ህክምና አገልግሎት
🔹የጥርስ ህክምና አገልግሎት
🔹ከአንገት በላይ ህክምና አገልግሎት
🔹የቆዳ ህክምና አገልግሎት
🔹የፊዚዮቴራፒ ህክምና አገልግሎት
🔹የራጅ (X-ray) ፣ የአልትራሳውንድ ፣ የሲቲ ስካን (CT-scan) ፣ የኤም.አር.አይ (MRI) ፣ የፓቶሎጂ እና የተለያዩ የላብራቶሪ ምርመራዎች አገልግሎት
የግል ህክምና አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቀናት ፦
🔹ከሰኞ እስከ ሐሙስ
➪ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ
🔹ዓርብ
➪ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ
🔹ቅዳሜ ፣ እሁድና የበዓል ቀናት
➪ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ
የግል ህክምና የምትፈልጉ ሁሉ በተጠቀሱት ቀናት እንዲሁም ሰዓታት ውስጥ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
አድራሻ ፦ አዲስ አበባ – ጉለሌ ክፍለ ከተማ – ወረዳ 1 – ከሽሮሜዳ ወደ እንጦጦ በሚወስደው መንገድ ላይ ያገኙናል።


Source: GetuTemesgen









No comments yet.