#Ethiopia | ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በተለይም በዓረብኛ ቋንቋ የሚሰነዘርባትን የተዛባ ትርክት ለመቀልበስ በምታደርገው ጥረት ውስጥ “ኪንግስ ኦፍ ዓባይ” የሚዲያ ተቋም የፈጠረው ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዲያው መሥራች ኡስታዝ ጀማል በሽር እና ጓደኞቹ የሚያከናውኑትን ሥራ ከሀገራዊ የዜና ተቋማት ጋር በማነጻጸር “ራሱን የቻለ ትልቅ ሚዲያ” ሲሉ ገልጸውታል።
ኪንግስ ኦፍ ዓባይ የውጭ ኃይሎች የሚፈሩት እና የሚያከብሩት ተቋም ቢሆንም በሀገር ውስጥ ግን ተገቢው ዕውቅና ሳይሰጠው መቆየቱን ጠቁመዋል።
ሚዲያው በዓረብኛ ቋንቋ የኢትዮጵያን እውነት በማስተጋባት የፈጠረው ንቅናቄ፣ የብዙዎችን ዐይን የገለጠ እና በሀገራችን ላይ ይሣል የነበረውን ስህተት የተሞላበት ምሥል የቀየረ መሆኑን ጠቁመው፣ መንግሥትም ሆነ እርሳቸውም ለዚህ ሥራው ታላቅ ክብር እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
“ስለ ኢትዮጵያ ማንነት ስህተት የሆነ ነገር ሲሣል፣ ምን እየተደረገ እንዳለም እንኳን አታውቅም ነበር” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኡስታዝ ጀማል እና ጓደኞቹ ይህንን ክፍተት በመሙላት ለሀገራቸው ትልቅ እገዛ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
በአንፃሩ ታዲያ ከሀገራቸው በተቃራኒ ቆመው አሉታዊ ነገሮችን ብቻ በማውራት ገንዘብ እየሠሩ ያሉ ወገኖች እንዳሉ አንሥተዋል።
ብዙዎች የውሸት ወሬ በመዝራት ገንዘብ ለመሰብሰብ ሲሮጡ፣ ኡስታዝ ጀማል ግን ጠልቆ በመግባት እውነታውን እንደሚያወጣ መስክረዋል።
“ሥራችሁ ወደ ፊት በዐርበኝነት የሚጠቀስ ነው” ሲሉም አወድሰዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያለው ሁሉ ጋዜጠኛ ነኝ በሚልበት በዚህ ዘመን፣ እንደ ኡስታዝ ጀማል ያሉ በሐቅ ላይ የቆሙ ባለሙያዎች ሙያቸውን ሊከላከሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
መንግሥት መረጃን ማዛባት በተመለከተ ግልጽ ፖሊሲ ቢኖረውም፣ አዳዲስ ሚዲያዎችን ላለማጥፋት ሲባል በማስፈጸም ረገድ ጥንቃቄ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።
ኪንግስ ኦፍ ዓባይ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ዙሪያ የጀመረው ሐቅን የታጠቀ የዲጂታል ዲፕሎማሲ እና የሚዲያ ተጋድሎ በመንግሥት ከፍተኛ ዕውቅና አግኝቷል።
በዮናስ በድሉ
Ethiopian Broadcasting Corporation #EBC #Ethiopia #PMAbiyAhmed #media #kingsofabay


Source: GetuTemesgen









No comments yet.