ኢራቅ እና ፓኪስታን ከኢራን ጋር የኢነርጂ ስምምነት ተፈራረሙ​ኢራቅ እና ፓኪስታን የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) ጭነቶች …

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢራቅ እና ፓኪስታን ከኢራን ጋር የኢነርጂ ስምምነት ተፈራረሙ
​ኢራቅ እና ፓኪስታን የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) ጭነቶች በሆርሙዝ ወሽመጥ በሰላም እንዲያልፉ ከኢራን ጋር ስምምነት ማድረጋቸውን Reuters ዘግቧል። ይህ እርምጃ ቴህራን በዓለም ቁልፍ በሆነው የባህር መስመር ላይ ያላትን ቁጥጥር እያጠናከረች መሆኑን ያሳያል።
ኢራቅ የበጀት ገቢዋን ለማስጠበቅ ሁለት ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች  — እያንዳንዳቸው 2 ሚሊዮን በርሜል የያዙ — በወሽመጡ በሰላም እንዲያልፉ ከኢራን ጋር ተስማምታለች።
​ ፓኪስታን ደሞ የበጋውን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት ከኳታር የሚመጡ ሁለት የጋዝ (LNG) ጫኝ መርከቦች እንዲያልፉላት ከኢራን ፈቃድ አግኝታለች።ኢራን በወሽመጡ የሚያልፉ መርከቦች ዝርዝር መረጃ (ሰነድ) እንዲያቀርቡ እና በባህር ኃይልዋ ቁጥጥር ስር እንዲጓዙ በማድረግ መስመሩን በይፋ እየተቆጣጠረችው ትገኛለች።
​ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ቁጥር ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከነበረው ወርሃዊ አማካይ (3,000 መርከቦች) ወደ 5% ዝቅ ብሏል። የዚህ መታገድ ተከትሎ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከ50% በላይ፣ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) ዋጋ ደግሞ ከ35–50% ጭማሪ አሳይቷል።
​ሌሎች ሀገራትም ተመሳሳይ ስምምነቶችን ለማድረግ ከኢራን ጋር ድርድር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2