#Ethiopia | በቤት ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራትን በጋራ በመካፈል እናቶችንና ሴቶችን መደገፍ እንደሚቻልና ይህም በአኗኗር ዘይቤ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ተሟጋች (ኢሰመተ) ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) እና ከኦክስፋም ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በየካ ክፍለ ከተማ (ወረዳ 10 እና 12) ለ180 ነዋሪዎች ላለፉት 6 ወራት የሰጠው ሥልጠና ተጠናቋል።
ይህ “” ሥልጠና ወንዶች በአመለካከትና በተግባር ተለውጠው የቤት ውስጥ ሥራዎችን ከባለቤቶቻቸው ጋር እንዲጋሩ ለማስቻል ያለመ ነው።
የስልጠናው ተጠቃሚዎች በሰጡት ምስክርነት፣ ወንዶች እንጀራ ከመጋገር ጀምሮ ልዩ ልዩ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ማገዝ መጀመራቸውንና ይህም በቤተሰብ ውስጥ የነበረውን ከፍተኛ የሥራ ጫና እና ድካም እንዳቀለለው ገልጸዋል።
በዕለቱ በተከናወነው በዚህ መርሃ-ግብር ላይ ለወረዳ አመራሮች፣ ለወጣቶች እና ለዕድሮች ምክር ቤት የዕውቅና ስጦታ ተበርክቷል።
እንዲሁም የቤት ውስጥ ሥራዎችን በመጋራት ለሌሎች አርአያ መሆን የቻሉ 15 ባሎች ልዩ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ



Source: GetuTemesgen









No comments yet.