የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ መጪው የዓረፋ በዓል በመተጋገዝ እና ለሀገር ሰላም ዱዓእ በማድረግ እንዲከበር

- Advertisement -
Sidebar AD

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ መጪው የዓረፋ በዓል በመተጋገዝ እና ለሀገር ሰላም ዱዓእ በማድረግ እንዲከበር ጥሪ አደረገ

#Ethiopia | ምክር ቤቱ የ1447ኛውን የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል ምክንያት በማድረግ ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼይኸ አብዱልከሪም ሼይኸ በድረ-ዲን በሰጡት መግለጫ፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በመረዳዳትና በመተጋገዝ ሊያከብረው እንደሚገባ እና ለሀገር ሰላም ዱዓ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል፡፡

በዓሉ የታማኝነት፣ የመስዋዕትነትና የትዕግስት እሴቶች የሚታወሱበት በመሆኑ፣ ሕዝበ ሙስሊሙ መንፈሳዊ ይዘቱን ጠብቆ ሊያከብረው እንደሚገባም አስታውሰዋል። በዚህም አቅመ ደካሞችን፣ ወላጅ አልባ ሕፃናትንና ሕሙማንን በመጠየቅና በመርዳት በዓሉን ማሳለፍ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የምክር ቤቱ የልማት እና ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ እንዲሁም ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ሼይኸ ሐሚድ ሙሳ በበኩላቸው፤ የሃይማኖቱን አስተምህሮ በማንሳት በዓሉ በተመሳሳይ መልኩ እንደሚከበር ገልጸዋል፡፡

አክለውም በየአካባቢው ያሉ ችግረኛ ወገኖችን ታሳቢ በማድረግና በመጠየቅ ማክበር እንደሚገባ አንስተው፤ የኢትዮጵያን የሰላም አማራጮች ማሳደግ እንደሚገባና ለዚህም በጋራ መሥራት እንዳለበት አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ስደት (ሂጅራ) የተከናወነባትና እንግዶቿን ያስተናገደችባት ምድር በመሆኗ በዓሉ ልዩ ያደርገዋልም ብለዋል፡፡

የዘንድሮው የ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል ነገ ረቡዕ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት መግለጹ ይታወቃል፡፡

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: