ቀደም ሲል በተለያዩ ምክንያቶች በተዘጉ የምርጫ ጣቢያዎች ለተመዘገቡ መራጮች በምርጫው ዕለት ልዩ የምዝገባና የማረጋገጫ ሂደት ተካሂዶላቸው ድምፅ እንዲሰጡ መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ቦርዱ ዛሬ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ውሳኔው የዜጎችን የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብት ለማስከበርና ሂደቱን አካታች ለማድረግ ታስቦ የተወሰነ ነው ብሏል።
ቦርዱ ከዚህ ቀደም ባደረገው የክትትልና የማጣራት ሥራ የሕግ ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል ያላቸውን 22 የምርጫ ጣቢያዎች አግዶ እንደነበር ይታወሳል።
እርምጃው የተወሰደባቸው እነዚህ ጣቢያዎች በ5 ክልሎች ማለትም፡- በኦሮሚያ 12፣ በሶማሌ 6፣ በሲዳማ 2፣ በአማራ 1፣ በሐረሪ ክልል 1 የምርጫ ጣቢያዎች ናቸው፡፡ የምርጫ ጣቢያዎቹ ሙሉ ለሙሉ ቢታገዱም፤ በእነዚህ የታገዱ ጣቢያዎች ውስጥ የተመዘገቡ ዜጎች መብታቸው ተጠብቆ በልዩ አሠራር ድምፅ የሚያስገቡበት ሁኔታ መመቻቸቱን ምርጫ ቦርድ ገልጾአል።
በፋሲል አረጋይ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.