” ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ ይደረጋል ” – ሚኒስቴሩ
“የመንገድ የትራፊክ አደጋን ለመግታት” አሽከርካሪዎች በዘመናዊ አሰራር ብቃታቸው እንደገና ሊመዘን እንደሆነ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አሳወቀ።
ሚኒስቴሩ፤ ” አሁን በስራ ላይ ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ በማድረግ ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል አጠቃላይ የሰነድ ዝግጅት ተጠናቋል ” ብሏል።
” ይህ አዲስ አሰራር ከተለመደው አሰራር በተለየ መልኩ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንደሆነና የምዘና ሂደቱ ከእጅ ንክኪ (የሰው ጣልቃገብነት) የጸዳ እንደሆነ ” አመልክቷል።
አሽከርካሪዎች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ቅድሚያ ስልጠና እንደሚወስዱና ከመጀመሪያው ምዝገባ ጀምሮ እስከ ስልጠናው ብሎም ምዘናና ሰርተፊኬሽን ድረስ ያለው አጠቃላይ ሂደት በዘመናዊ ሲስተም እንደሚመራ ነው ሚኒስቴሩ ያመልከተው።
ይህን ስራ ለመስራት ሚኒስቴሩ SDS Safety & Driving Skills ከተባለ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር የስራ ውል ስምምነት መፈረሙን አሳውቋል።
ሁሉም አሽከርካሪዎች አዲሱን የብቃት ምዘና በመውሰድ እና በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ብቃታቸውን በተጨባጭ በማረጋገጥ ብቻ እንዲያሽከረክሩ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት እንደሚዘረጋም ተነግሯል።
ሚኒስቴሩ ” ሁሉም አሽከርካሪ በዚህ ሂደት የሚያልፍ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይ ለዚህ ዙር በቅድሚያ ማንኛውም የንግድ ተሽከርካሪ የሚያሽከረክር አሽከርካሪ የምዝገባና የስልጠና እንዲሁም የምዘና ሂደቱ በቅርቡ ስለሚጀመር ዝግጁ እንዲሆን ” ሲል አሳስቧል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.