#Ethiopia | በአሜሪካዊቷ ድምጻዊት ታይለር ስዊፍት ኮንሰርት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የሞከረው ግለሰብ የ15 አመት እስራት ተቀጣ።
እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2024 አሜሪካዊቷ ድምጻዊት ታይለር ስዊፍት በቤና ኮንሰርት ለማቅረብ በሄደችበትና ሌሎች የአሜሪካ ሙዚቀኞች በነበሩበት ያልተጠበቀ ጥቃት ለመሰንዘር የሞከረው የ21 አመቱ ኦስትሪያዊ ወጣት የ15 አመት እስራት ተፈርዶበታል።
ቤራን ኤ የተባለው ግለሰብ ፥በኦስትሪያ የግላዊነት ህጎች መሰረት በሌሎች ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዙ ወንጀሎችም ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱ ተነግሯል።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው በቬና ኧርነስት ሃፕል ስታዲየም፥ የመጀመሪያው የ ታይለር ስዊፍት ኮንሰርቶች ሊደረግ ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ፥ ከሲአይኤ በደረሰ ጥቆማ መሰረት መሆኑ ተመላክቷል።
ይህንንም ተከትሎ ወደ 2መቶ ሺ የሚጠጉ የታይለር ስዊፍት አድናቂዎች የተሰባሰቡበት ኮንሰርት ወዲያውኑ እንዲሰረዝ ተገዷል።
አቃቤህግ እንዳስታወቀው፥- ተከሳሽ ቤራን ኤ ጽንፈኛ ሆኖ መገኘቱን እና የጂሃዲስት እስላማዊ መንግስት (አይ ኤስ) ተላላኪ መሆኑን አምኗል።
የፍርድ ቤት የስነ-አእምሮ ሃኪም የሆኑት ፒተር ሆፍማንም፥ ቤራን ኤ ምንም አይነት የአእምሮ ህመም እንደሌለበት መረጋገጡን ገልጸዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#NBC #Ethiopia #BBC
Source: GetuTemesgen









No comments yet.