#Ethiopia | የፓሪሰን ዠርሜን (PSG) የሻምፒዮናነት ድልን ተከትሎ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ እና በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ስርዓት አልበኝነት እስካሁን 416 ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከታሰሩት ደጋፊዎች መካከል 283ቱ በፓሪስ ከተማ ውስጥ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ ድርጊቱን ለማስቆም በነበረው ግጭት ሰባት የፖሊስ አባላት ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።
የክለቡ ደጋፊዎች በደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው አራት ዋና ዋና የቀለበት መንገዶችን ለመዝጋት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን፥ በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ የነበረው የእልልታና የደስታ አገላለጽ እስከ ንጋት ድረስ ቀጥሎ አድሯል።
በሌላ በኩል ፒኤስጂ ይፋዊ የዋንጫ ድሉን በፓሪስ በሚገኘው “Champ-de-Mars” ክፍት የሕዝብ መናፈሻ በጎዳና ላይ እንደሚያከብር ታውቋል።
በዚህ ታላቅ የጎዳና ላይ የድል ክብረ በዓል ላይ እስከ 90,000 የሚደርሱ የክለቡ አድናቂዎችና ነዋሪዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#PSG #Paris #Ligue1 #FootballNews #France #BreakingNews
Source: GetuTemesgen








No comments yet.