#Ethiopia | ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በመሆን ያገለገሉት አምባሳደር ዓሊ አብዶ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት በሕይወት መለየታቸው ተሰምቷል።
የአምባሳደር ዓሊ አብዶ የቀብር ሥነ ሥርዓት የቤተሰቦቻቸው፣ የቅርብ ወዳጆቻቸውና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ከጁምዓ ሶላት በኋላ በዳለቲ ሙስሊሞች መቃብር ሥፍራ ይፈጸማል።
በአርሲ ዴረ ከተማ ከአባታቸው ከአቶ ዓሊ ሱለይማንና ከእናታቸው ከወይዘሮ አፀደ ወልደማሪያም የተወለዱት አምባሳደር ዓሊ፣ ባለትዳርና የሦስት ሴቶች እንዲሁም የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ።
ከ1990 እስከ 1995 ዓ.ም ባሉት ዓመታት መዲናዋን የመሩት አምባሳደር ዓሊ አብዶ፣ 27ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በመሆን ማገልገላቸው ይታወሳል። በሥራ ዘመናቸውም አገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት፣ በታማኝነትና በትጋት ማገልገላቸው ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለአምባሳደር ዓሊ አብዶ ጀነተል ፊርደውስን፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው ሕዝብ ደግሞ መጽናናትን ተመኝቷል።
#አምባሳደርዓሊአብዶ #አዲስአበባ #የቀብርሥነሥርዓት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen








No comments yet.