በኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ የሕይወት ተሞክሮ ላይ የሚያተኩር አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአይናለም አዱኛ (ዶክተር) የተሰናዳውና በውጭ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕይወትና ተግዳሮቶች ላይ የሚያጠነጥነው “Walking Between Worlds: Letter to the Next Generation of the Ethiopian Diaspora” የተሰኘው መጽሐፍ በይፋ ተመርቋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት በተከናወነው የገበያ ማቅረቢያ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፣ ታዋቂ ምሁራን፣ ዳያስፖራዎችና በርካታ የክብር እንግዶች ታድመዋል።

በዕለቱም በምሁራንና በተሳታፊዎች አማካኝነት ስለ ዲያስፖራው ማኅበረሰብ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

ለአምስት አሥርት ዓመታት ገደማ (ከ38 ዓመታት በላይ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት የኖሩት ደራሲዋ ዶክተር ዓይናለም አዱኛ፣ መጽሐፉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸው ስለ አገራቸው በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸውና የሚጠበቅባቸውን አገራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በስደት ዓለም ያሳለፉትን የረጅም ጊዜ የሕይወት ተሞክሮና ገጠመኝ መሠረት በማድረግ ያዘጋጁት ይህ መጽሐፍ ለሌሎች ወገኖች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑንም አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ በበኩላቸው በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ ዶክተር ዓይናለም ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን በጎ ተግባር ማከናወናቸውንና እንዲህ ዓይነቱ አበረታች ሥራ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ ባለ 480 ገጽ ሆኖ ለንባብ መብቃቱ ታውቋል።

#Diaspora #EthiopianDiaspora #BookLaunch #AAU #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: