በአዲሱ በጀት ዓመት የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ይደረግ እንደሆነ በግልጽ እንዲታወቅ ተጠየቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ ዓመት 25ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የፌደራል መንግስትን የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጥያቄያቸውን ለምክር ቤቱ ካቀረቡት አባላት መካከል የአብን (የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ) ፓርቲን ወክለው የምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ይገኙበታል።
ዶክተር ደሳለኝ በጥያቄያቸው፤ መንግስት ለ2019 በጀት ዓመት ለመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ያደርጋል ወይ? የሚለው ጉዳይ በግልጽ እንዲታወቅ ጠይቀዋል።
የምክር ቤት አባሉ ጥያቄውን ባቀረቡበት ወቅት ባለፈው ዓመት የታዘቡትን አጋጣሚ በማስታወስ፤ “ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጥያቄ ለምክር ቤቱ አቅርቤ ‘የደመወዝ ጭማሪ የለም’ የሚል ምላሽ ከተሰጠኝ ከአንድ ወር በኋላ ጭማሪ ተደርጓል” ብለዋል። በመቀጠልም “ዘንድሮስ ጭማሪ የለም ካሉኝ ከአንድ ወር በኋላ ጭማሪ ይኖራል ወይ?” ሲሉ በሚኒስትሩ አገላለጽ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ በፈገግታ የታጀበ ጥያቄ በማስከተል ሰንዝረዋል።
ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፤ መንግስት ቀደም ሲል በሁለት ዙር የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉን ጠቅሰዋል።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በክልሎች በኩል በፐርሰንት ተሰርቶ የቀረበው የደመወዝ ጭማሪ ተመን እና ለጉዳዩ ከተመደበው በጀት ጋር ባለመመጣጠኑ ምክንያት፣ አሁንም ድረስ ተጨማሪ የማጥራትና የማስተካከል ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ለአባላቱ አስገንዝበዋል።
@Seledadotio

No comments yet.