#FastMereja I ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከተ እየተበባሰ የመጣው የቅብዓት እምነት አራማጆችን በተመለከተ የችግሩ አሳሳቢነት ከዕለት ወደዕለት እየተበባስ ስለሆነ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ደብዳቤ ጻፉ።
በተለይም በቆጋ ገዳም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሾሞናል በማለት ጥቅምት 17/2010 ዓ.ም ህገወጥ ሹመት በፈጸሙት ግለሰቦች ላይ ቅዱስነትዎ እና ቅዱስ ሲኖዶስ የማያዳግም ውሳኔ እንዲሰጥብት ደጋግመው አሳስበዋል።
ጳጳሱ በመግለጫቸው፣ በቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ መሠረት “የቅባት” ትምህርት እንደ ስህተት መታየቱን በማስታወስ፣ ጉዳዩን በዝርዝር አስረድተዋል።
ብፁዕ አቡነዘካርያስ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት የፀና መሆኑን ጠቅሰው፣ በቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ መሠረት “የቅባት” ትምህርት ከቅዱስ መጽሐፍ እና ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና ውጭ መሆኑን ገልጸዋል።
አባ ዘካርያስ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔዎች በመጥቀስ፣ ከዚህ ቀደም የነበሩ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ይህንን አስተምህሮ በስህተትነት እንደፈረጁት ያስታወሱ ሲሆን፣ አሁንም በዚሁ መሥመር መታዘዝ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በቤተክርስቲያኒቱ ስም አዲስ ትምህርት እያስተማሩ የሚገኙትን አካላት በተመለከተ፣ ሊቀ ጳጳሱ ምዕመናን ከዚህ አስተምህሮ እንዲርቁ ጥሪ አቅርበዋል። በተለይም፣ “የቅባት” ትምህርት ተከታዮች የሚጠቀሙባቸው ጥቅሶች ከዐውዱ ውጪ የተተረጎሙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ይህንን ድርጊት “ሕገ-ወጥ” ሲሉ ገልጸውታል።
ሰነዱ፣ ቀደም ሲል በቤተክርስቲያኒቱ የተወሰኑ ውሳኔዎች ተላልፈው እንደነበርና አሁን ላይም የዚህ ውሳኔ አፈጻጸም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መከታተል እንደሚገባ ያሳያል። በተጨማሪም፣ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ በሀገረ ስብከታቸው ሥር የሚገኙ አገልጋዮች እና ምዕመናን በቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ አስተምህሮ ብቻ እንዲጓዙ መመሪያ ሰጥተዋል።
Source: FastMereja







No comments yet.