አሜጋ የብድርና ቁጠባ ማህበር በወቅታዊ የመኪና ዋጋ መናር ምክንያት ለተጠቃሚዎች በከፊል ያገለገሉ መኪኖችን ለመግዛት የሚያስችሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

አሜጋ የብድርና ቁጠባ ማህበር በወቅታዊ የመኪና ዋጋ መናር ምክንያት ለተጠቃሚዎች በከፊል ያገለገሉ መኪኖችን ለመግዛት የሚያስችሉ አዳዲስ የብድር አማራጮችን ይፋ ማድረጉን አስታወቀ።

#FastMereja I አሜጋ የብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር፥ በገበያ ላይ የሚታየውን የአዳዲስ መኪኖች ዋጋ መናር ተከትሎ፣ ያገለገሉ መኪኖችን መግዛት ለሚፈልጉ አባላቱ አዲስ የብድር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በዛሬው እለት በጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

ማህበሩ ቀደም ሲል ለኤሌክትሪክ መኪና ግዢ ብድር የወሰዱ አባላቱን መኪኖች ያስረከበ ሲሆን፥ በዋጋ መጨመር ምክንያት በወቅቱ ማስረከብ ባይችልም ከደንበኞቹ ጋር ባደረገው ስምምነት ችግሩን መፍታቱንና ተረካቢዎቹም ተገቢውን ቁጠባ እያከናወኑ መስተናገዳቸውን ገልጿል።

የማህበሩ አመራሮች ከብድር ወሳጆችና በሂደት ላይ ካሉ አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት፣ ያጋጠሙ የአሰራር ችግሮችንና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከቦርድ አባላት ጋር ምክክር አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ማህበሩ ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለመሆንና አማራጮችን ለማስፋት ሶስት አዳዲስ የብድር አገልግሎቶችን አዘጋጅቷል።

እነዚህም ያገለገሉ መኪኖችን ለመግዛት የሚረዳ የቤት መኪና ብድር፣ ቤት ለመስራት፣ ለመጠገንና ለመግዛት የሚያስችል የቤት ብድር፣ እንዲሁም በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩና ስራቸውን ማስፋፋት ለሚፈልጉ የሚሰጥ የስራ ብድር ናቸው።

ማህበሩ የሚዲያ እና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ከሚያከናውኗቸው ስራዎች ጋር በማገናኘት ልዩ የብድር አገልግሎት እያቀረበ መሆኑን አስታውቋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: