የዶናልድ ትራምፕ ምስል የተካተተበት ፓስፖርት አገልግሎት ላይ ሊውል ነው።

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካን 250ኛ ዓመት ልደት ለመዘከር በቀረቡ የፓስፖርት ንድፎች ላይ የትራምፕን ፎቶግራፍ አካተተ።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አርብ ዕለት በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አዲሱን የፓስፖርት ገፆች የሚያሳይ ንድፍ ያጋሩ ሲሆን፤ ፓስፖርቱ የአሜሪካን የነፃነት እወጃ ከጀርባቸው ያደረገ የራሳቸውን ፎቶራፍ እና ፊርማን ያካተተ ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እንዳለው ፓስፖርቱ በሚቀጥለው ሳምንት ለዜጎች ይቀርባል።

አዲሱ ፓስፖርት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የፌደራል ሕንፃዎች፣ ድረ ገፆች እና ሰነዶችን ጨምሮ የአገሪቱ ተቋማት ላይ የራሳቸው ስም እና ምሥል በመለጠፍ እያደረጉት ያለው ተከታታይ እርምጃ የቅርቡ ነው።

“የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ አዲስ ፓስፖርት እንኳን ደኅና መጣችሁ፤ ነገር ግን መልካም ሁኑ ይላል” ሲሉ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

“እንኳን ደኅና መጣችሁ፤ ነገር ግን መልካም ሁኑ” የሚለው ፅሁፍ ትራምፕ ባገሩት የፓስፖርቱ ገፅ ላይ አይታይም።

በኤክስ ገፁ ላይ የትራምፕን ልጥፍ ያጋራው ዋይት ሐውስ አዲሱን ሰነድ “የአርበኛ ፓስፖርት” ብሎታል።

የአዲሱ ሰነድ አቅርቦት አሁን ላይ የተገደበ እና ፓስፖርቱ ለአሜሪካ ዜጎች ብቻ የቀረበ ነው።

ይህን ፓስፖርት ለማግኘት አሜሪካዊያን በበይነ መረብ ወይም በፖስታ ቤት ማመልከት አይችሉም።

እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ፓስፖርቱ የሚገኘው ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ የፓስፖርት ማዕከል በአካል በመቅረብ ብቻ ነው።

በተመረጡ የልደት በዓሉን በሚዘክሩ ሁነቶች ላይም ማመልከቻዎች እንደሚከፈቱ ቢቢሲ ጠቁሟል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#አሜሪካ #ዶናልድትራምፕ
#ፓስፖርት #ቢቢሲዜና
#ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgenmediacommunication


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1