#Ethiopia | የብሪታንያ መንግሥት የጥገኝነት ፈቃድ ለሰጣቸው ስደተኞች ከዚህ ቀደም ላወጣባቸው ወጪና ላደረገላቸው ልዩ ልዩ ድጋፎች የሚሆን ገንዘብ መልሶ ሊያስከፍል ማቀዱን አስታውቋል።
በዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች መረጃ እንደሚያመለክተው ይህ አዲስ አሠራር ጥገኝነት ያገኘ ማንኛውም ስደተኛ በሀገሪቱ ውስጥ ሰርቶ ገቢ ማግኘት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን እያንዳንዱ ግለሰብ 10 ሺህ ፓውንድ መልሶ እንዲከፍል ይደረጋል። ይህ ሕግ በቀጥታ የሚተገበረው በብሪታንያ ምድር ውስጥ በሕጋዊ መንገድ የመሥራት መብት ባላቸው ሰዎች ላይ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።
ስደተኞቹ በሀገሪቱ ውስጥ በቋሚነት የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት የሚችሉት ይህንን የተወሰነባቸውን የገንዘብ መጠን ሙሉ በሙሉ ከፍለው ሲያጠናቅቁ ብቻ ነው።
ይሁን እንጂ ክፍያውን ለመጀመር ስደተኞ ሊኖራቸው የሚገባው አነስተኛው የወርሃዊ ገቢ መጠን ምን ያህል መሆን እንዳለበት እስካሁን በይፋ የተጠቀሰ ነገር የለም።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.