የአዲስ አበባ ልጅ ሜላት ኪሮስ በአሜሪካ ኮንግረስ እጩ ሆና ቀረበች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ዲሞክራቲክ ሶሻሊስቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊት መላት አስፋውወሰን ኪሮስ በኮሎራዶ ግዛት 1ኛ የኮንግረስ ዲስትሪክት በተካሄደው የዲሞክራቲክ ፓርቲ የመጀመሪያ ደረጃ የዕጩነት ምርጫ የ15 ዘመን ተመራጯን አንጋፋዋን ዲያና ዲጌትን በማሸነፍ አስደናቂ ታሪካዊ ድል አስመዝግባለች።

አሶሺየትድ ፕሬስ ውድድሩን ውጤት ይፋ ባደረገበት ዘገባ መሠረት ይህች የ29 ዓመቷ የሕግ ባለሙያና የፒኤችዲ ተማሪ ሜላት በአሜሪካ ኮንግረስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጄን ዜድ (Gen Z) የዚህ ትውልድ ሴት ተመራጭ እንድትሆን አስችሏታል።

ውድድር የተደረገበት ዲስትሪክት ሙሉ በሙሉ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጠንካራ ይዞታ በመሆኑ ሜላት በመጪው ምርጫ አሸንፋ በሚቀጥለው ዓመት ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደምትቀላቀልና እሷ በተወለደችበት በ1997 ዓ.ም ሥልጣን የያዙትን የ68 ዓመቷን ዲጌትን እንደምትተካ በእርግጠኝነት ይጠበቃል።

​ይህ ያልተጠበቀ ድል በዲሞክራቲክ ፓርቲ ውስጥ ወጣትና ይበልጥ ወደ ግራ ዘመም አዳዲስ ዕጩዎች አንጋፋዎቹን የፖለቲካ መሪዎች በመገዳደር ሥልጣን እንዲያስረክቡ እያደረጉት ባለው ውስጣዊ የፖለቲካ ንቅናቄ ውስጥ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

እስራኤል ደጋፊ ቡድኖች የሚመጣን ማንኛውንም የገንዘብ ድጋፍ በቆራጥነት የገፋችው ሜላት ሁለንተናዊ የጤና እና የሕፃናት እንክብካቤን ጨምሮ ለአይሁድ መንግሥት የሚሰጠውን የአሜሪካ ወታደራዊ እርዳታ ማቆምን የመሳሰሉ ጠንካራና አነጋጋሪ ፖሊሲዎችን ታራምዳለች።

ይህ ድል የአሜሪካ ዲሞክራቲክ ሶሻሊስቶች በሀገሪቱ ያስመዘገቡትን ተከታታይ ስኬት ይበልጥ ያጎላው ሲሆን በምርጫው ስታሸንፍ በኮንግረስ ውስጥ ጥቂት ከሆኑት ዲሞክራቲክ ሶሻሊስቶችና ትውልድ ተወካይ በመሆን ለወጣቶችን ልዩ ነገር ትፈጥራለች ተብሎ ይጠበቃል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2