#Ethiopia | በአሜሪካ ኖርዝ ካሮላይና ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ ስሜቴ ያዘዘኝን በማድረጌ የአንድ ሚሊየን ዶላር አሸናፊ ሆኛለሁ ማለታቸውን ዩፒአይ ዘግቧል።
አሸናፊው ላውሪንበርግ በሚገኝ አንድ መደብር ውስጥ በድንገት የገዙት የጭረት ሎተሪ ትኬት ያልጠበቁትን ድል እንዲቀዳጁ አድርጓቸዋል።
ስለ ድሉ ሲናገሩም ያንን ትኬት እንድገዛ የሆነ ነገር ውስጤ ነገረኝ ያ ስሜት በወቅቱ ጠንካራ ነበር በማለት በውስጣዊ ስሜታቸው መታመናቸው አሸናፊ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል።
ያሸነፉትን የገንዘብ ክፍያ በአንድ ጊዜ መቀበልን በመምረጣቸው ከታክስ በፊት 600,000 ሺህ ዶላር ከታክስ በኋላ ደግሞ 432,000 ሺህ ዶላር በእጃቸው አስገብተዋል።
አሸናፊው ይህንን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለቤተክርስቲያናቸው ድጋፍ እንደሚያበረክቱት ተናግረዋል ብሎ የፃፈው ዩፒ አይ ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#NorthCarolinalottrywinner
#CashwordKingscratch
Source: GetuTemesgen









No comments yet.