ሩስያ እየነደደች ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

*ሴንት ፒተርስበርግ በዩክሬን ድሮኖች ጭስ በጭስ ሆናለች።

#Ethiopia | ዩክሬን በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በሚገኝ ቁልፍ የነዳጅ ማከማቻ ተቋም ላይ የድሮን ጥቃት አድርሳለች።

ጥቃቱ በባህር ዳርቻው የሚገኘውን የሴንት ፒተርስበርግ የነዳጅ ተርሚናልን በከፍተኛ ደረጃ የጎዳ ሲሆን በቦታውም ትልቅ የእሳት አደጋ ተቀስቅሷል።

የሩሲያ ባለስልጣናት በአካባቢው ከ70 በላይ ድሮኖች መተው መጣላቸውን ገልጸዋል።

ከነዳጅ ማከማቻው በተጨማሪ በባህር ኃይል ጣቢያ ላይም ሌላ ጥቃ መድረሱ ታውቋል።

የዩክሬን መንግስት ጥቃቱ የሩሲያን የጦር መሣሪያ አቅም የሚደግፈውን ኢኮኖሚ ለማዳከም ያለመ መሆኑን አሳውቋል።

የዩክሬን ጥቃት ተከትሎ ከሩስያ በኩል እስካሁን ድረስ ምንም የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።

ሆኖም ክሬምሊን ለዚህ ጥቃት ተመጣጣኝ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ተንታኞች እየገለፁ ይገኛሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#SaintPetersburg #oilterminal
#Ukrainiandrones


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1