በሳዑዲ ዓረቢያ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን የሞት ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ መሆኑ ተዘገበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሳዑዲ ዓረቢያ የተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ወደ 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሞት ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ የMiddle East Eye ዘገባ አመልክቷል።

እንደ ዘገባው፣ በእስር ላይ ያሉ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን በዓረብኛ ቋንቋ የተዘጋጀና ይዘቱን በውል ያልተረዱትን የጥፋተኝነት ሰነድ እንዲፈርሙ መገደዳቸውን ለዜና ተቋሙ በሚስጥር መናገራቸው ተጠቅሷል። ይህም በእስረኞቹና በቤተሰቦቻቸው መካከል ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ ተነግሯል።

በተጨማሪም፣ በካሚስ ሙሻይት እስር ቤት ብቻ 58 ኢትዮጵያውያን መታሰራቸውን የጠቀሰው ዘገባ፣ ባለፈው ሚያዝያ ወር ሦስት ኢትዮጵያውያን ላይ የሞት ቅጣት መፈጸሙንም አስታውሷል።

ጉዳዩ በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ የዲፕሎማሲና የሰብዓዊ መብት ጥረቶች እንዲጠናከሩ ጥሪ እያቀረበ ነው። ይሁን እንጂ እነዚህ ክሶች በሳዑዲ ባለሥልጣናት በይፋ ስለመረጋገጣቸው ወይም ስለመሰጠቱ ምላሽ በዘገባው አልተገለጸም።

#Ethiopia #SaudiArabia #HumanRights #EthiopianMigrants #MigrantCrisis


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: