“ገንዘብ በሩን ይከፍትልህ ይሆናል፤ ዕውቀት ግን የተከፈተውን በር ተከፍቶ እንዲቆይ ያደርግልሃል”

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የገንዘብ ነጻነትንና ዘላቂ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ከሁሉ በላይ በፋይናንስ ዕውቀት ላይ መዕዋለ ንዋይን ማፈሰስ ወሳኝ መሆኑ ቶኒ ኤሉሜሉ ገልጸዋል ።

እንዴት መቆጠብ፣ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስና ጥበብ የተሞላበት የፋይናንስ ውሳኔዎችን ማድረግ እንደሚቻል መረዳት ከተወሰነ ደመወዝ ወይም ጊዜያዊ የፋይናንስ እድል በላይ የሚሻገሩ ዘላቂ እድሎችን ይፈጥራል።

​የቶኒ ኤሉሜሉ ፋውንዴሽን መሥራች ቶኒ ኤሉሜሉ እንደሚሉት እውነተኛ ማደግ የሚሆነው ሰዎች ዘላቂ ብልፅግናን መገንባት የሚያስችላቸውን ዕውቀት ሲታጠቁ ነው።

እርሳቸው ሰዎች አዲስ ክህሎት በመማር፣ የተሻለ የፋይናንስ ውሳኔ በመወሰንና ለተሻለ ነገ አንድ እርምጃ በመራመድ የሕይወት ለውጥ እንዲያመጡ ጥሪ አቅርበዋል ፤ ምክንያቱም ዕውቀት ከተግባር ጋር ሲጣመር ዘላቂ ለውጥና እድገት ይከተላልና ባይ ናቸው።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1