#FastMereja | የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ከወሊሶ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ታሪካዊ የስራ ስምምነት ተፈራረመ። የስምምነቱ ዋና ዓላማ የዓድዋው ተጋድሎ ጀግና የደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶን ታሪክ እና አኩሪ ገድል የሚያወሳውን ታሪካዊ የመድረክ ቴአትር በጀግናው የትውልድ ስፍራ በሆነችው ወሊሶ ከተማ ለህዝብ እይታ ለማቅረብ ነው።
ከክቡር ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ ቤተሰቦች ጋር በተደረገ የጠበቀ ቅንጅት እና ትብብር እውን የሆነው ይህ ስምምነት፣ ቴአትሩን በስፍራው ለመድረክ ለማብቃት ከማስቻሉም በላይ በወሊሶ ከተማና አካባቢው የኪነ-ጥበብ ዘርፍን በስፋት ለማስተዋወቅ እና ለማሳደግ ትልቅ መሰረት ይጥላል። ሁለቱ አካላት በተደረሰው ስምምነት መሰረት በጉጉት የሚጠበቀውን ይህንን ታላቅ ቴአትር በቅርቡ ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚያቀርቡ ሲሆን፣ የጀግኖችን አገራዊ ውሎ በኪነ-ጥበብ ህያው በማድረግ ለተካኪው ትውልድ የማስተላለፍ ስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።



Source: FastMereja









No comments yet.