አስደንጋጭ ጥናት፡ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያሴቶች ሚስትን መደብደብን እንደሚያጸድቁ ተገለጸየኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግ…

- Advertisement -
Sidebar AD
አስደንጋጭ ጥናት‼️፡ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ
ሴቶች ሚስትን መደብደብን እንደሚያጸድቁ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ይፋ ባደረገው አዲስ የዴሞግራፊ እና የጤና ዳሰሳ ጥናት፤ ከግማሽ በላይ (55 በመቶ) የሚሆኑ ሴቶች ባል ሚስቱን ለመደብደብ አሳማኝ ምክንያት ይኖረዋል ብለው እንደሚያምኑ አመላክቷል። ምግብ ማቃጠል፣ መጨቃጨቅ እና ልጆችን ችላ ማለትን ጨምሮ በተዘረዘሩ አምስት ሁኔታዎች ዙሪያ የተደረገው ይህ ጥናት፣ ሚስትን ለመምታት በቂ ምክንያት እንዳለ የሚያስቡ ወንዶች ቁጥር 39 በመቶ መሆኑንና ከቀድሞው ጋር ሲነጻጸር በ11 በመቶ መጨመሩን ገልጿል።
በሌላ በኩል፣ ትምህርት እና የቤተሰብ ገቢ ሲጨምር ይህንን አዝማሚያ የመቀበል አመለካከት እየቀነሰ እንደሚሄድ ጥናቱ ያሳያል። ከሁለተኛ ደረጃ በላይ ትምህርት ካገኙ ሴቶች መካከል እንዲህ የሚያስቡት 29 በመቶው ብቻ ሲሆኑ፤ በሲዳማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ከፍተኛው ቁጥር ሲመዘገብ፣ ሶማሌ ክልል ዝቅተኛውን አሃዝ አስመዝግቧል። የቤት ውስጥ ጥቃትን ተገቢ የሚያደርጉ አመለካከቶችን ለመለወጥ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማጠናከር እና የግንዛቤ ሥራዎችን ማስፋፋት እንደ ዋና መፍትሔ ተቀምጧል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1