ብድር ያጎበጠው አል ናስር

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የሳውዲ አረቢያው ሀያል ክለብ አል ናስር ለፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአራት ዓመታት ውስጥ 625 ሚሊዮን ዶላር የከፈለ ቢሆንም በምላሹ ግን ማግኘት የቻለው አንድ ዋንጫ ብቻ ነው።

ይህንን እጅግ ከፍተኛ ክፍያ ተከትሎ ክለቡ በአሁኑ ወቅት የ280 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ ውስጥ የገባ ሲሆን አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ደግሞ ክለቡ ይፋ ያደረገው ሩቡን ነው የዕዳው መጠንም ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር እየተጠጋ ነው ብለዋል።

​ይህንን የፋይናንስ ቀውስ ተከትሎ የሳውዲ አረቢያ የሕዝብ ኢንቨስትመንት ፈንድ በአል ናስር ላይ ጥብቅ ገደቦችን ጥሏል።

በዚህም ምክንያት የክለቡ አጠቃላይ የፋይናንስ ሁኔታ እስካልተፈታ ድረስ አል ናስር ምንም ዓይነት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም እንዳይችል ተከልክሏል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: