ከግንባታ ቦታ የወጡ ተሽከርካሪዎች መንገድን በጭቃ በማበላሸታቸው 55 ሺህ ብር ተቀጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በሚገኘው አሮጌ ቄራ አካባቢ የሚገኘው TNT Construction የግንባታ ፕሮጀክት ተሽከርካሪዎች መንገድን በጭቃ በማበላሸታቸው 55 ሺህ ብር ቅጣት እንደተጣለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አስታውቋል።

እንደ ባለሥልጣኑ መረጃ፣ የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች ድርጊቱን ከፈጸሙ በኋላ በወቅቱ የነበረውን ዝናብ ተገን በማድረግ ከቦታው ለመሰወር ቢሞክሩም፣ የአራዳ ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት ከልደታ ትራፊክ ማኔጅመንት ጋር በመተባበር ተሽከርካሪዎቹን በመለየት 55 ሺህ ብር የአስተዳደራዊ ቅጣት ጥሏል።

ባለሥልጣኑ ተቋማት ሥራቸውን ሲያከናውኑ የሕዝብ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች፣ የመንገድ መሠረተ ልማቶች፣ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን በጥንቃቄ በመጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል።

በተጨማሪም የክረምት ወቅት በመሆኑ ለማህበረሰቡ አደጋ የሚያስከትሉ ወይም የመሠረተ ልማት ጥበቃን ችላ የሚሉ የግልና የመንግሥት ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ የሕግ ማስከበር እርምጃዎች በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥሉ ገልጿል።





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: