ተፃፈ በመሐሪ ነጋሽ
(የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኮሚኒኬሽን )
#Ethiopia | ዛሬ ማምሻውን የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ልዑክ ቡድናችንን በከፍተኛ ኩራትና በመልካም ምኞት ወደ አሜሪካ ኦሪገን ሸኝተናል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶቻችን በተሟላ ዝግጅት ወደ ሻምፒዮናው እንዲያቀኑ ሱሉልታ በሚገኘው የጀግናው ኦሊምፒያን አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሆቴል በማሳረፍ አስፈላጊውን ድጋፍ፣ ክትትልና ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።
የቀነኒሳ በቀለ ሆቴልም አትሌቶቻችንን እንደቤተሰቦቹ በመቀበል፣ በፍቅር፣ በአክብሮትና በልዩ እንክብካቤ እስከ ሽኝታቸው ድረስ አግዟቸዋል።
ለዚህ ውድ አስተዋፅኦ ከልብ የመነጨ ምስጋና ተቀበሉ
ዓለም የሚጠብቀው ሻምፒዮና 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች (World Athletics U20 Championships) ሻምፒዮና ….
በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ በሚገኘው ታሪካዊው ሄይዋርድ ፊልድ ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3 ይካሄዳል።
ከ1,700 በላይ ወጣት አትሌቶች ከ190 የሚጠጉ አገራት በ44 የውድድር ዓይነቶች ላይ ይፎካከራሉ።
ዩጂን ከተማ በግምት 180,000 የሚጠጋ ህዝብ ያላት ብትሆንም፣ በዓለም ላይ “Track Town USA” በሚል ስም የምትታወቅ የአትሌቲክስ ዋና መዲና ናት።
የሻምፒዮናው ትኬቶች በፍጥነት እየተሸጡ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፣ ውድድሩም በብዙ የዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ኔትወርኮች፣ ዲጂታል መድረኮች እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የስፖርት ጋዜጠኞች ይሸፈናል። የዚህ ውድድር ቀደምት እትሞች በ140 በላይ አገራት በቴሌቪዥን ተሰራጭተው 16 ሚሊዮን በላይ የተጠራቀመ የቲቪ ተመልካች ደርሰው ነበር።
በ2024 በፔሩ ሊማ በተካሄደው 20ኛው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 6 የወርቅ፣ 1 የብር እና 2 የነሐስ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ በአጠቃላይ 9 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በዓለም 2ኛ ደረጃን ማስመዝገቧ ይታወሳል።
ዘንድሮም አትሌቶቻችን በ5000 ሜትር፣ 3000 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 800 ሜትር፣ 3000 ሜትር መሰናክል፣ 400 ሜትር እና በርምጃ ውድድሮች ላይ የኢትዮጵያን ስም በክብር ለማስጠራት ዝግጁ ናቸው።
ለጀግኖቻችን…
ውድ አትሌቶቻችን!
ከእናንተ ጋር የሚጓዘው የኢትዮጵያ 60 ዓመታትን ያስቆጠረ የድል ታሪክ ነው፤ የአበበ ቢቂላ ጨምሮ
የብዙ ጀግኖች የድል አሻራ ነው።
ኢትዮጵያውያን ልብ ከእናንተ ጋር ነው። በእግራችሁ የምትሮጡት ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችሁ፣ ለሕዝባችሁ እና ለመጪው ትውልድ ነው።
መልካም ጉዞ!
መልካም ውድድር!
መልካም ዕድል! 🇪🇹❤️



Source: GetuTemesgen









No comments yet.