የሼክ መሐመድ አልአሙዲ ሀብት 10.1 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ፤ በብሉምበርግ የዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር 375ኛ ደረጃን ያዙ
የትውልደ ኢትዮጵያዊው ባለሀብት ሼክ መሐመድ አልአሙዲ የተጣራ ሀብት 10.1 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ተከትሎ በብሉምበርግ የዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ በድጋሚ ተካተዋል።
ዛሬ ኦገስት 1፣ 2026 ይፋ በሆነው የብሉምበርግ ዝርዝር መሠረት፣ አልአሙዲ በዓለም 375ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በ2026 ብቻ የሀብታቸው መጠን በ1.67 ቢሊዮን ዶላር፣ ወይም በ19.7 በመቶ አድጓል። በቅርብ ጊዜም በአንድ ቀን ብቻ 33.7 ሚሊዮን ዶላር መጨመሩ ተመዝግቧል።
የብሉምበርግ ግምገማ እንደሚያሳየው፣ የአልአሙዲ ሀብት መጨመር ከኢነርጂ፣ ከኢንዱስትሪ፣ ከመሠረተ ልማት እና ከሌሎች የንግድ ንብረቶቻቸው ዋጋ መጨመር ጋር የተያያዘ ነው። ከዚህ ቀደም ከዋና ንብረቶቻቸው መካከል የነበረው የስዊድኑ ፕሪም (Preem) የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ ግን ለVARO Energy ከተላለፈ በኋላ በአሁኑ ጊዜ VAROPreem በተባለ የተዋሃደ ኩባንያ ስር ይገኛል።
በሌላ በኩል፣ ብሉምበርግ የአልአሙዲን ሀብት ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደደረሰ ቢገልጽም፣ በፎርብስ 2026 ዓመታዊ የዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ግን ስማቸው አልተካተተም። ይህም ሁለቱ ተቋማት የቢሊየነሮችን ሀብት በሚገምቱበት የመረጃ ምንጭና የግምገማ ዘዴ ልዩነት መኖሩን ያሳያል።
በብሉምበርግ የወጣው አዲሱ መረጃ የሚያመለክተው፣ ሼክ መሐመድ አልአሙዲ ከቀደሙት ዓመታት የሀብት መቀነስ በኋላ በድጋሚ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሀብት ደረጃ መመለሳቸውን ነው።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.