የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ አይናቸውን ወደ ሰሜን አሜሪካ አድርገዋል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ዳንጎቴ በአፍሪካ እና በሰሜን አሜሪካ መካከል ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ውይይት ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር አድርገዋል።

አሊኮ ዳንጎቴ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር የኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል ነው የተባለው።

ዳንጎቴ አፍሪካ ያላትን ያልተነካ የተፈጥሮ ሀብት፣ እያደገ የመጣ የሸማች ቁጥር እና ሰፊ የገበያ ዕድል ለካናዳ መንግሥት እና ባለሃብቶች አስተዋውቀዋል።

የዳንጎቴ ግሩፕ እና ሌሎች አፍሪካውያን ባለሃብቶች በካናዳ ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን መንገድ በተመለከተም ተወያይተዋል።

እንዲሁም የካናዳ ኩባንያዎች በአፍሪካ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱበትን ስትራቴጂያዊ ሁኔታዎች አንስተዋል ተብሏል።

ዳንጎቴ በአፍሪካ እና በካናዳ መካከል የሚደረግ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዘላቂ እድገትን ለማምጣት ከፍተኛ አቅም አለው ብለዋል።

የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለመጨመር ፈጠራን ለማበረታታት እና ለሁለቱም ወገኖች ጠቃሚ የሆኑ የንግድ ግንኙነቶችን ለመገንባት ጠንካራ ምክንያት አለን ሲሉ ነው የተናገሩት።

አሊኮ ዳንጎቴ አፍሪካውያን ባለሃብቶች በራሳቸው አህጉር ላይ በግንባር ቀደምትነት መዋዕለ ንዋያቸውን ማፈሰስ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ይህም ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች ወደ አፍሪካ ገበያ ለመግባት ያላቸውን እምነት እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#NorthAmerica #Africa
#Dangote #business
#investment


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2