ዳናዊት መክብብ በፍትሐብሔር ክስ በነፃ ተሰናበተች

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I የታዋቂዋ የቲቪ ፕሮግራም አቅራቢና የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዳናዊት መክብብ ቀርቦባት የነበረው የፍትሐብሔር ክስ ውድቅ ተደርጎ በነፃ የተሰናበተች ሲሆን፣ ከእሷ ጋር በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች አራት ተከሳሾች ግን ጥፋተኛ ተብለው ገንዘብ እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ አራተኛ ፍትሐብሔር ችሎት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ፣ አምስተኛ ተከሳሽ ሆና የቀረበችው ዳናዊት መክብብ የንግድ ፈቃድ አይታ የማስታወቂያ ሥራ የሰራች በመሆኗ በጉዳዩ ላይ ልትጠየቅ አይገባም በሚል ከክሱ በነፃ አሰናብቷታል።

ጉዳዩ የተጀመረው 13 ከሳሾች «ወደ ውጭ ሀገር እንልካችኋለን» በሚል ከእያንዳንዳቸው 437 ሺህ ብር የተቀበላቸው የኤቢኤል ኮንሰልታንሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ የቤተልሔም ታደሰ፣ ገሊላ በለጠ፣ አቤል ተስፋዬ እና የዳናዊት መክብብ ክስ በመስረታቸው ነው። ከሳሾቹ የተወሰደብን ገንዘብ እንዲመለስልን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ተከሳሾቹ ሊመልሱልን አልቻሉም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አብራርተው ነበር።

እንደ ኢትዮጲካሊንክ ዘገባ ለወራት ክሱን ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤቱ፣ አራቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በነጠላና በአንድነት የተወሰደውን ገንዘብ ለከሳሾቹ እንዲከፍሉ ሲወሰን፣ ዳናዊት መክብብ ግን በነፃ ተሰናብታለች።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1