#FastMereja I በሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ውድድር ከመድረክ ፊት ለፊት ከሚታዩት ውበቶች እና ተወዳዳሪዎች ባሻገር፣ ላለፉት ዘጠኝ ተከታታይ ዓመታት ከመድረክ ጀርባ በመሆን ፕሮግራሙ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ሙያዊ አስተዋጽኦ ያበረከተው ወጣት ዘውዱ የኔነህ ነው።
በኢትዮጵያ የውበት እና የፋሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ስም ባለው በሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ውድድር ላይ ከመድረክ ጀርባ የሚከናወኑ የፕሮዳክሽን፣ የፎቶግራፍ እና የዝግጅት ስራዎች ለፕሮግራሙ ውበትና ጥራት ወሳኝ ድርሻ አላቸው። ወጣት ዘውዱ የኔነህ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት የፕሮዳክሽን ማኔጀር በመሆን የፕሮግራሙ ሂደት ሳይስተጓጎል በስኬት እንዲመራ፣ የታቀዱ ሁነቶች በሰዓታቸው እንዲከናወኑ እና ምስላዊ ውበቱ ተጠበቆ ለህዝብ እንዲደርስ ሲሰራ ቆይቷል።
ከሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ዝግጅት ጎን ለጎን የFocus Studio ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ የሆነው ዘውዱ፣ በፎቶግራፍ እና በቪዲዮ ፕሮዳክሽን መስክ የራሱን ዘመናዊ አሻራ ማሳረፍ ችሏል። የውድድሩ ተሳታፊዎች በመድረክ ላይ የሚያሳዩት በራስ መተማመን እና የሚታየው ድንቅ ውጤት ከመድረክ ጀርባ ባሉ እንደ ዘውዱ ባሉ ትጉህ ባለሙያዎች ድካም እና ሌሊት ከቀን ጥረት የሚገነባ መሆኑን የዘጠኝ ዓመታት ዘላቂ አገልግሎቱ ማረጋገጫ ሆኗል።
Source: FastMereja









No comments yet.