“የኢኮኖሚ ጦርነት” ማወጅ ነው፦ ሩስያ
#Ethiopia | የአሜሪካ ሴኔት በሩሲያ የኃይል ዘርፍ ላይ አዲስና ጠንካራ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ረቂቅ ህግ አፀደቀ።
ከዩክሬን ጦርነት ጀምሮ ሞስኮ የተለያዩ ምዕራባውያን ማዕቀቦችን በመሸሽ ነዳጇን በቅናሽ ዋጋ ለሌሎች ሀገራት ስትሸጥ ቆይታለች።
አሁን የፀደቀው አዲሱ ህግ ይህንን ቀዳዳ ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት ያለመ ነው ተብሏል።
ህጉ በሩሲያ ላይ ብቻ ሳይሆን ከሩሲያ የኃይል ኩባንያዎች ጋር ማንኛውንም የንግድ እና የገንዘብ ልውውጥ በሚያደርጉ ሀገራት እና ኩባንያዎች ላይ ጥብቅ እገዳ ይጥላል።
የሩሲያን የነዳጅ ሽያጭ የሚያመቻቹ ዓለም አቀፍ ባንኮች ከአሜሪካ የፋይናንስ ስርዓት እና ከዶላር ዝውውር እንዲገለሉ ያደርጋል ነው የተባለው።
ክሬምሊን ህጉን የኢኮኖሚ ጦርነት ማወጅ ስትል የኮነነችው ሲሆን የነዳጅ ምርቷን ሙሉ በሙሉ ወደ እስያ እና አፍሪካ አዳዲስ ገበያዎች ለማዞር እንደምትሰራ አስታውቃለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Russia #usa #Ukraine
#Sanctions #OPEC
#Market #economy
Source: GetuTemesgen









No comments yet.