ኢትዮጵያ ያወጣሁትን ወጪ ትክፈለኝ! ~ ደቡብ አፍሪካ

- Advertisement -
Sidebar AD

*ደቡብ አፍሪካ ለዜጎቻችሁ ያወጣሁትን ወጪ መልሱልኝ ስትል ኢትዮጵያ ናይጄሪያና ማላዊን ጠየቀች

#Ethiopia | የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ሰፊ ቁጥር ያላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የሚገኙባቸው ሀገራት የመልሶ ማቋቋሙን የፋይናንስ ጫና አብረው ሊጋሩ እንደሚገባ አሳስቧል።

በደቡብ አፍሪካ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የተጠየቀበትን ቀነ ገደብ ተከተሎ በተነሳው ተቃውሞና ውጥረት በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸውን በነጻ ፍቃድ እና በዲፖርቴሽን ወደ ሀገራቸው መመለስ መጀመራቸው ይታወሳል።

የደቡብ አፍሪካ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ዋና ዳይሬክተር ቶሚ ማኮዴ ለፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ በሰጡት ማብራሪያ ሀገራቸው እያካሄደች ባለችው የስደት እና የመልሶ ማቋቋም ስራ 292 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርጋለች ብለዋል።

ይህ በድንገት የወጣ በጀት በመሆኑ
ፕሬዝዳንቱ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሦስቱ ሀገራት ወጪው እንዲተኩ የሚገልጽ ደብዳቤ በኤምባሲዎቻቸው አማካኝነት እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።

ደቡብ አፍሪካ ይህንን ገንዘብ ወጪ ያደረገችው ሰነድ አልባ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ጊዜያዊ ማዕከላት ለማጓጓዝ ለተከራዩ አውቶቡሶች የተከፈለ ነው ብላለች።

በተጨማሪም ዜጎቹ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ መንግስት ለከፈተው ጊዜያዊ መጠለያ የወጣ ገንዘብ መሆኑን ገልጻለች።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#SouthAfrica #Parliament
#Emigrants #Ethiopia #Nigeria
#repatriationcosts


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: