ሁለቱ አፈ ታሪኮች ዳግም ተገናኙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አዲሱ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ፋቢያን ባርቴዝ የብሔራዊ ቡድኑ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ።

የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና አዲሱ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን የቡድኑን የቴክኒክ አባላት ይፋ ሲያደርጉ የቀድሞው ድንቅ ግብ ጠባቂ ፋቢያን ባርቴዝ የብሔራዊ ቡድኑ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙ ተረጋግጧል።

በ1998 የዓለም ዋንጫን እና በ2000 የአውሮፓ ዋንጫን ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ያሳኩት ዚነዲን ዚዳን እና ፋቢያን ባርቴዝ በድጋሚ በብሔራዊ ቡድኑ ዳግም ተገናኝተዋል።

ባርቴዝ የዲዲዬ ዴሻምፕስ የ14 ዓመታት የኃላፊነት ዘመን ሲጠናቀቅ ፍራንክ ራቪዮትን በመተካት የግብ ጠባቂዎች ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሾሟል።

ዚዳን በሪያል ማድሪድ ቤት አብሮት የነበረውን ዳቪድ ቤቶኒን ረዳት አሰልጣኝ አድርጎ የሾመ ሲሆን አጠቃላይ 23 አባላት ያሉት የስልጠና እና የህክምና ቡድን ይፋ ተደርገዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Francenatinal #footballTeam
#ZinedinZidan #FabianBartez


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1