በከባድ ዝናብ አማካኝነት ጃፓን ውስጥ ስድስት ሰዎች ሞተዋል ተባለበምስራቅ ጃፓን ቺባ ግዛት ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ ቢያንስ ስድስ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በከባድ ዝናብ አማካኝነት ጃፓን ውስጥ ስድስት ሰዎች ሞተዋል ተባለ
በምስራቅ ጃፓን ቺባ ግዛት ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ ቢያንስ ስድስት ሰዎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን፤ አምስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
የጃፓን ባለሥልጣናት ‹‹ታይቶ የማይታወቅ›› ሲሉ የገለጹት ዝናብ፤ ከ20 ሺህ በላይ አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ሲቀንስ፣ 7 ሺህ ተጓዦች ደግሞ በቶኪዮ ናሪታ አየር ማረፊያ በአንድ ሌሊት በረራቸው እንዲዘገይ አድርጓል።        
ይህ የጎርፍ አደጋ የተከሰተው በዚህ ሳምንት በጃፓን እና በአጎራባች አገሮች ውስጥ ተከታታይ አውሎ ነፋሶች ከተከሰቱ በኋላ ነው።
የጃፓን የሜትሮሎጂ ኤጀንሲ እንደገለጸው፤የቅርብ ጊዜውን የጎርፍ አደጋ ያመጣው ወደ አገሪቱ ምሥራቅ የሚፈሰው ሞቃታማና እርጥበት አዘል አየር ሲሆን፤ይህም ከላይ ካለው ቀዝቃዛ አየር ጋር ተዳምሮ የከባቢ አየር ሁኔታን እጅግ ያልተረጋጋ ያደርገዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: