የጤና ሚኒስቴር የሄፐታይተስ ‘ቢ’ ቫይረስን ስርጭት ለመከላከል ከ15 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች በሀገር አቀፍ ደረጃ ክትባት ሊሰጥ እንሆነ አስታወቋል።
ክትባቱ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ እንዳለው ለአሐዱ ሬዲዮ የተናሩት የሚኒስቴሩ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ፍቃዱ ያዴታ ናቸው፡፡
ከ1999 ዓ.ም. በኋላ ለተወለዱ የሄፐታይተስ ‘ቢ’ ቫይረስ በደማቸው መኖር አለመኖሩን በምርመራ በማረጋገጥ ክትባት መውሰድ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በተለይ የጤና ባለሙያዎች ለበሽታው ከፍተኛ ተጋላጭ በመሆናቸው ክትባቱን እና ምርመራውን ሊወስዱ ይገባል ተብሏል።
በስራ ሂደቱ የሚያጋጥመው ዋነኛ ችግር የሀብት እጥረት መሆኑን ዶክተር ፍቃዱ ገልጸዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ከሔፒታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር እንደሚኖር ቢታወቅም የህክምና አገልግሎቱን በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ማድረግ እንዳልተቻለ ዶ/ር ፍቃዱ አስታውሰው፤ ኢትዮጵያ ካላት ሰፊ የቆዳ ስፋት አንፃር የህክምና ማዕከላትን በአንድ ጊዜ ተደራሽ የማድረግ አቅሟን እያጠናከረች ትገኛለች ብለዋል፡፡
#አሐዱ_ሬዲዮ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.