ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኔዓለም በሴቶች መግቢያ በኩል ባለው ሙዳየ ምጽዋት አጠገብ ቆሞ፣ ሁሉን በሚያውቅ ባህርይው ስጦታውንና ስጦታው የተሰጠበትን ልብ ያይ ነበር። አንዳንዶች ለዝና ሰጡ፣ ሌሎች ስጦታቸውን ኑሮአቸውን ሊያናጋ እንደማይችል በማሰብ ሰጡ።
አንዲት ድሃ መበለት ግን በቤትም በእጇም የነበራትን ሁለት ሳንቲም በሙሉ ሰጠች። ከእነዚህ ከሁለት ሳንቲሞች ውጪ በምድር ላይ ምንም ጥሪት ሀብት የላትም። በዚህ ጊዜ ጌታ “እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድሃ መበለት ከሁሉ አብልጣ ጣለች እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሔር መዝገብ ጥለዋልና ይህች ግን ከጉድለቷ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች” አለ፡፡ ይህ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 21፣1-4 የሰፈረው ይህ ቃል የመስጠትን ምንነት ጌታችን በሚገባ ያስረዳበት ነው፡፡ ሁሉ የእርሱ ሲሆን በቸርነትና በልግስና ከሰጠው ላይ ስጡኝ ብሎ ይለምናል፡፡
የዚህች መበለት በጌታችን የተደነቀ መስጠት ብዙ ይነግረናል፡፡ አለማስተዋል እንጂ እንኳን ገንዘባችን እኛ ራሳችን ዋጋ የተከፈለብን የእግዚአብሔር ገንዘቦች ነን።
አንዳንዶቻችን ከሰጠን የሚጎድልብን እየመሰለን እንሰስታለን፣ እግዚአብሔር ግን ስጡኝና ፈትኑኝ፣ የጎደለውን ባልሞላ በረከቱን ባላበዛ ታዘቡኝ ይለናል። ደግሞም ስጦታ ከጉድለት እንጂ ከትርፍ አይደለም።
ስጦታችን ካልተሰማን ገና አልሰጠንም ማለት ነው። እናም ማትረፍ ከፈለግን ከጉድለታችንም ቢሆን በፍቅር እንስጥ። በተለይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ክረምቱን እያሳለፈ ላለው ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም።
ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም” በከባድ ንፋስና ዝናብ ምክንያት ቤተ መቅደሱ ፈርሶ ይገኛል፣ መነኮሳቱም በድርቅና በርሃብ ከባድ ፈተና ውስጥ ሆነው ድጋፋችንን እየጠበቁ ነውና የድጋፍ እጃችንን እንዘርጋላቸው።
ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡- 1000766349227
አቢሲንያ ባንክ ፡- 262281132
ለበለጠ መረጃ:- 0944672222 ወይም 0916106921
Source: Yeneta Tube








No comments yet.