እኛ : የት እንጠብቅህ?

- Advertisement -
Sidebar AD

ዳዊት : ”አራዳ ማዞሪያ”

#Ethiopia | ​በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከትያትሪካል አርትስ ት/ት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘውና በባለብዙ ዘርፍ የጥበብ ስራዎቹ የሚታወቀው ዳዊት ተስፋዬ አዲስ የቪዲዮ ፕሮግራም ይዞ ከመጣ ሰነባብቷል።

ዳይሬክተር፣ የፊልም ጸሐፊ ፣ ገጣሚ እንዲሁም ፖድካስተር ዳዊት ተስፋዬ ከዚህ ቀደም አርቲስት ብርቱካን የተሳተፈችበትንና የተለየ ሃሳብ ይዞ ብቅ ያለውን “ዘጠኝ ሞት” የተሰኘ የፊልም ስራ ለተመልካች ማቅረቡ ይታወሳል።

በርካታ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ባፈራው አቶቢስ ተራ አድጎ ለሀገሪቱ የጥበብ ዘርፍ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኘው ዳዊት “ደጃፍ ቲቪ” በተሰኘው የዩቲዩብ ቻናሉ አማካኝነት “ደጃፍ ፖድካስት” የተሰኘ ዝግጅት ሲያቀርብ ቆይቷል።

በደጃፍ ፖድካስት ከተለያዩ የሙያ መስኮች የተወጣጡ እንግዶችን በመጋበዝ የህይወት፣ የኑሮ እና የሥራ ልምዶቻቸውን ለተመልካች የሚያካፍልበትን መድረክ ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

​በአሁኑ ወቅት “ደጃፍ ፖድካስት” ዕረፍት ላይ መሆኑን ተከትሎ ዳዊት ተስፋዬ ፤ ከዘላለም ምፅላል ፋንቱ እና ከአለኝታ ለገሰ ጋር በመሆን “አራዳ ማዞሪያ” የተሰኘ አዲስ ዝግጅት በዚሁ ቻናል ላይ ጀምሯል።

“It’s all about perspective” በሚል መሪ ቃል የተዋቀረው ይህ አዲስ ፕሮግራም በየሳምንቱ አነጋጋሪና ሞቅ ያሉ አጀንዳዎችን በማንሳት አንዳ’ንዴም ከእንግዶች ጋር ሰፊ ውይይት የሚደረግበት እና የተለያየ አመለካከት የሚስተናገድበት ነው።

ተመልካቾችም አዲሱን “አራዳ ማዞሪያ” ዝግጅት በደጃፍ ቲቪ መከታተል የሚችሉ ሲሆን ለዳዊትና ለስራ ባልደረቦቹም በዚሁ አዲስ ዝግጅታቸው ስኬትን እንመኛለን።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1