#Ethiopia | በአሜሪካዋ ኦሬጎን ግዛት በተካሄደው የዓለም የ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3,000 ሜትር መሰናክል ውድድር አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ የተቀዳጀችው አትሌት አልማዝ ዮሐንስ በአዲስ አበባ የሲዳማ ኮሚኒቲ ማህበር አዘጋጅነት ደማቅ የእንኳን ደስ አለሽ አቀባበል ተደረገላት።
በዚህ የክብር መርሃ ግብር ላይ የከተማዋ የሲዳማ ተወላጆች፣ የማህበሩ አመራሮች እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ አትሌቷ ያስመዘገበችው ይህ ታላቅ ድል የሀገሪቱን ታላቅ የስፖርት አቅም ያሳየና ሙሉውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያስደሰተ መሆኑ ተገልጿል።
በዝግጅቱ ወቅት ባህላዊ የክብር አቀባበል የተከናወነ ሲሆን፣ ማህበሩ ለአትሌቷ የምስጋና እና የእውቅና ስጦታዎችን አበርክቶላታል።
አትሌት አልማዝ ዮሐንስ በበኩሏ የተደረገላት ይህ ድንቅ አቀባበልና ማበረታቻ ለቀጣይ የስፖርት ጉዞዋ ትልቅ ሀይልና መነሳሳት እንደሚሆናት ገልጻ አመስግናለች።
አትሌቷ በቀጣይ ወደ ሀዋሳ ከተማና ወደ ትውልድ ስፍራዋ አርበጎና ስትጓዝም ተመሳሳይ ስፋት ያለው ደማቅ አቀባበል ይደረግላታል ተብሎ ይበልጣል።
#AlmazYohannes #WorldU20 #EthiopianAthletics #GoldMedal #SidamaCommunity #EthiopianSport #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.