‎​ኑ በዚጊቲው ተራራ ደብረ ታቦርን በጋራ እናክብር

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​የደብረ ታቦር ተራራ ምሳሌ ወደሆነችው ቤተ ክርስቲያን በመምጣት የደብረ ታቦርን በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ አቅራቢያ በሚገነኘው በዚጊቲ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን እናክብር በዚጊቲው ተራራ ላይ እንደ ታቦር ተራራ በፀሐይ ልናበራ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ጨርሰናል።

‎♦️ ​ደብረ ታቦር (ቡሄ)

‎​ደብረ ታቦር ማለት በግዕዝ ቋንቋ «የታቦር ተራራ» ማለት ሲሆን፣

‎♦️ ​«ደብር» ማለት ተራራ

‎​«ታቦር» ደግሞ በቅዱስ መጽሐፍ የሚታወቅ የአንድ ተራራ ስም ነው።

‎♦️ ​የተራራው ትርጉም፦
‎«ደብር» ተራራ ሲሆን «ታቦር» ደግሞ በገሊላ ምድር የሚገኝ ረጅም ተራራ ነው

‎♦️​የብርሃን መገለጫ፦

‎የደብረ ታቦር በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ክብሩን እና ፊቱ እንደፀሐይ ያበራበት የተቀደሰ ተራራ መሆኑን ያሳያል።

‎♦️ ​የቡሄ በዓል፦

‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን «የቡሄ በዓል» ተብሎ የሚከበረው ይህንን ክስተት በማስታወስ ነው።

‎​ዚጊቲ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን (አርባ ምንጭ)

‎የተለያዩ ዝማሬዎችን ቃለ ወንጌል እና በቤተክርስቲያኑ የሚደረጉ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮችን ለመከታተል

‎👉 YouTube
‎ https://www.tiktok.com/@abomedia05?_r=1&_t=ZS-98lmTgdJZi9

‎👉 tiktok https://www.tiktok.com/@abomedia05?_r=1 ‎ይከታተሉ

Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2