#Ethiopia | በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ውስጥ እንዲሳተፉ በተደረጉ 62 ዜጎቿ መገደላቸውንና የ15ቱ ደብዛ መጥፋቱን የገለጸችው ጋና በሀገሯ ዜጎች ላይ የሚካሄደው ህገ-ወጥ የወታደር መልመላ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቀረበች።
የጋናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሙኤል ኦኩዜቶ አብላክዋ በሞስኮ ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ባደረጉት ውይይት ጉዳዩን በስፋት ያነሱ ሲሆን የሩሲያ ወገን በበኩሉ በጦርነቱ የሚሳተፉ የውጭ ሀገር ዜጎች በሰራዊቱ ውስጥ የሚቀላቀሉት በገዛ ፈቃዳቸው ውል በመፈረም እንደሆነ ምላሽ ሰጥቷል።
በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የሶስት ቀናት የጋና ልዑካን ቡድን የሞስኮ ጉብኝት የሚመሩት አብላክዋ ከጸጥታው ጉዳይ ባሻገር ከሩሲያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር የሚያጠናክሩ ውይይቶችን አድርገዋል።
በዚህም መሠረት ሩሲያ ለጋና ተማሪዎች የምትሰጠውን ዓመታዊ የነፃ ትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) ከ120 ወደ 240 ከፍ በማድረግ እጥፍ ያደረሰችው ሲሆን ትኩረቱም ፣በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፣ በኢንጂነሪንግ፣ በፔትሮሊየም ሳይንስ እና በፋርማሲዩቲካልስ ዘርፎች ላይ እንደሚሆን ታውቋል።
በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እንዲሁም ጋና ለሰላማዊ ዓላማ ልታውለው ባቀደችው የኒውክሌር ኃይል ልማት ዙሪያ አብሮ የመሥራት ሁኔታዎችን እያመቻቹ ይገኛሉ።
📸 DW
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.