የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የግል አብራሪ ልጅ አዲስ አበባ ገቡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የአሜሪካ የንግድ ሚኒስቴር ምክትል ረዳት ሚኒስትር ማርክ ሚቸል በአዲስ አበባ ባደረጉት ጉብኝት የአባታቸው የቀድሞ መስሪያ ቤት ጎብኝተዋል።

ምንም እንኳን ጉብኝቱ ለምክትል ረዳት ሚኒስትሩ የመጀመሪያቸው ቢሆንም ለቤተሰባቸው ግን ከሰባት አስርት ዓመታት በፊት የጀመረ ታሪካዊ ትስስር አለው።

​ከ75 ዓመታት በፊት የእሳቸው አባት ራልፍ ፍሊንት ሚቸል ጁኒየር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪ እንዲሁም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የግል አብራሪ ሆነው ያገለግሉ ነበር።

በወቅቱም ንጉሠ ነገሥቱን እቴጌይቱንና የቤተ መንግሥቱን ውሻ ጭምር በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉዞዎች ላይ ያጀቧቸው ሲሆን እንደ እ.ኤ.አ በግንቦት 1950 የተከናወነውን የአባይ ወንዝ ድልድይ የምርቃት ሥነ ሥርዓት ጨምሮ በርካታ ጉዞዎችን በክብር መርተዋል።

​ምክትል ረዳት ሚኒስትር ማርክ ሚቸል በአዲስ አበባ ባካሄዷቸው ስብሰባዎች ወቅት ይህ የቆየ የቤተሰብ ታሪክ በድጋሚ ህያው ሆኖ የቀረበ ሲሆን ይህም የሁለቱን ሀገራት ዘላቂ አጋርነት የሚያስታውስ አጋጣሚ ሆኗል።

ልክ እንደ ረጅም የአየር በረራ ሁሉ የአሜሪካና የኢትዮጵያ ግንኙነትም ጊዜንና ትውልድን ተሻግሮ ሩቅ የተጓዘናየጸና ለመሆኑ ይህ ክስተት ትልቅ ማሳያ ነው።

📸 US embassy Addis Ababa

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: