#Ethiopia | የቴክኖሎጂ እድገት ከሰዎች የግል ነፃነት እና ደህንነት ጋር በተያያዘ ስጋቶችን በደቀነበት በዚህ ወቅት በአሜሪካዋ ኒውዮርክ ግዛት በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ታሪካዊ ውሳኔ ተ አስተላለፈ።
በግዛቷ በሚገኙ ማናቸውም የፍርድ ቤት ግቢዎችና ችሎቶች ውስጥ ስማርት መነጽሮችን ይዞ መግባትና መጠቀም ሙሉ በሙሉ ታግዷል።
ይህም ኒውዮርክን መሰል ውሳኔ ያስተላለፈች የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ግዛት ያደርጋታል።
የዚህ እርምጃ ዋነኛ ዓላማ በችሎት ሂደት ላይ የሚሳተፉ ሰዎችን የግል ደህንነት መጠበቅና ያለፈቃድ የሚደረጉ ምስጢራዊ የድምፅና የምስል ቀረጻዎችን መከላከል ነው።
በህጉ መሠረት በፍርድ ቤት ውስጥ ያለፈቃድ ፎቶም ሆነ ቪዲዮ መቅረጽ በጥብቅ የተከለከለ ቢሆንም የቅርብ ጊዜዎቹ ስማርት መነጽሮች ግን ያለ ምንም ጥርጣሬ በምስጢር የመቅረጽ አቅም ስላላቸው አዲስ ስጋት ፈጥረዋል።
ምንም እንኳን መሣሪያዎቹ ምስል በሚቀርጹበት ወቅት የሚበራ የማስጠንቀቂያ መብራት ቢኖራቸውም በሶፍትዌር ማስተካከያ መብራቱን አጥፍቶ ምስጢራዊ ቀረጻ ማካሄድ እንደሚቻል ተደርሶበታል።
በአዲሱ ደንብ መሠረት ስማርት መነጽሮችን ማድረግ ብቻ ሳይሆን ይዞ ወደ ፍርድ ቤት ሕንጻ መግባትም የተከለከለ ነው።
ይህም የዕይታ ማስተካከያ የተገጠመላቸውን ጨምሮ ሁሉንም የስማርት መነጽር ዓይነቶች የሚያጠቃልል ሲሆን የታገዱት ተጠቃሚዎች በተራ የዕይታ መነጽሮች ተክተው እንዲመጡ ሕጉ ያስገድዳል።
ይህ የቴክኖሎጂ ምቾት ለይዘት ፈጣሪዎች ተመራጭ ቢሆንም ከግል ነፃነት አንጻር የደቀነው ስጋት ከፍተኛ በመሆኑ የኒውዮርክ ውሳኔ ለሌሎች ግዛቶችም አርአያ እንደሚሆን ይገመታል።
#SmartGlasses #NewYorkCourts #PrivacyRights #TechNews #LegalUpdate #CyberSecurity #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen








No comments yet.