እየጨመረ የመጣውን የኩላሊት ህመም ለመግታት የሚረዳው ፕሮጀክት ይፋ ሆነ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:-በኩላሊት ህሙማን የተቋቋመው “ተስፋ የኩላሊት ታካሚዎች ማህበር” የራሱን ዘመናዊ የኩላሊት እጥበት (ዲያሌሲስ) ማዕከል ለማቋቋም የሚያስችለውን የአዋጭነት ጥናት ማጠናቀቁንና ለዚህም ህብረተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ።

ማህበሩ በዛሬዉ እለት የ2018 ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን የፕሮጀክት ስራ አስኪያጁ አቶ በሃይሉ ኢረና እንደገለጹት፤ ህመሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ አደጋውን ለመግታት ማዕከሉን ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።

በጥናቱ መሰረት የሚቋቋመው ማዕከል 220 የአዋቂ እና 20 የህፃናት የዲያሌሲስ ማሽኖች የሚኖሩት ሲሆን፤ የግንባታ ወጪው 70 በመቶ በባንክ ብድር፣ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ ከሚሰበሰብ ገቢ እንደሚሸፈን ተገልፆ ማህበሩ በሂደት የራሱን ህንፃ የመገንባት አላማ ያለው ሲሆን፣ መንግስት የግንባታ ቦታ በነፃ እንደሚሰጠው እምነት እንዳለው አስታውቋል።

ማህበሩ “10 ብር ለኩላሊት እጥበት” በተባለው የገቢ ማሰባሰቢያ አማካኝነት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በዳሽን ባንክ በሚገኘው 3136 አጭር የሂሳብ ቁጥር ህብረተሰቡ፣ አጋር ድርጅቶችና በጎ ፈቃደኞች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

በምዝገባ ቁጥር 4008 በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበውና 23ዐ አባላት ያሉት ይህ ማህበር፤ በ2018 በጀት ዓመት ለ85 አባላቱ በወር4,000.0ዐ ብር የህክምና ድጋፍ በማድረግ የእጥበት ሂደታቸው እንዳይቋረጥ ማድረጉን ገልጿል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2